Home (ዋና ገጽ)
ICT (ቴክኖሎጂ ክፍል)
images

ስለእኛ

በአቴንስ የምንገኝ እና በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማራን፣ የተለያየ ልምድ ያለን እና በአንድ ላይ በመደራጀት ቀድሞ ስንሰራቸው የነበሩ ሥራዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማካሄድ የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያን ነን፡፡

ይህን የተቀናጀ የንግድ አገልግሎት ስንሰራ ከዕቃ ከአምራቾች የሚሰጠንን ማበረታቻ እና ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የምናተርፈውን ስጦታ ታሳቢ በማድረግ የተቋቋምን እንጂ በተጠቃሚ ደንበኞቻችን ላይ ተጨማሪ ዋጋ ወይም ድብቅ ሂሳብ የመያዝ ዓላማ የለንም፡፡

Why choose us/ለምን እኛን ይመርጣሉ?

እኛ ጋር አብረው ሊሰሩ ወይም ግዢዎትን ሊያከናውኑ ሲመርጡን በርግጥም ምክንያት አለዎት!

አዲስ አስተሳሰብ እና አሠራር

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች በዘመናዊ እና አዲስ አሰራር የተቃኑ ናቸው፡፡ ለሁሉም አምቺ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለማገልገል ሁልጊዜም እንጥራለን፡፡

በጥራት እና በአስተማማኝነት

ስውር ዋጋ አለመጨመር ወይም የተሳሳተ ሥራ አለመሥራት፣ አልያም ጥራት የሌለው ዕቃን ላለመሸጥ መሪ መርሃችን ነው፡፡

በመግባባት እና በእርስዎ ምርጫ ብቻ

ለቤተክርስቲያን አገልጋይ ደንበኞቻችን ምንሰጠውን የንዋያተ ቅድሳት እና ሌሎች ምርቶችን ወደ መረጡት ዓለም ክፍል የምንልክልዎ፣ በመጀመሪያ ከእርስዎ ጋር ተወያይተን ስንወስን ብቻ ነው፡፡

እንዴት እናገለግልዎታለን?

አገልግሎታችን መንፈሳዊ መሠረት ያለውና ለቤተክርስቲያን በሚጠቅም መልኩ እንዲሆን ዓላማችን ነው፡፡

ገዢን ከዕቃው ጋር ማገናኘት

ገዢዎቻችን ወደ ግሪክ ሀገር መምጣት ሳይጠበቅባቸው፣ እኛ ከምናቀርብላቸው ምርቶች በመምረጥ ወይም በራሳቸው ምርጫ ፈልገው እንድንልክላቸው በሚያዝዙን ጊዜ በታዛዥነት እንሠራለን፡፡ ደንበኞቻችን ያዝዙና፣ እኛ ምርቶችን ከማምረቻቸውና ከመደብራቸው በአስተማማኝ ሁኔታ መርጠን እንልካለን፡፡ በተጨማሪም ያለንን ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ በመጠቀመ ጥቅል የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ ደንበኞቻችን የተሻለውን ንዋይ ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንዲመርጡ እና የተለያዩ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እናማክራለን፤ ደንበኛውን ከሚፈልገው ዕቃ እና ጥራት ጋር እናገናኛለን፡፡ 

ዕቃዎችን መሰብሰብ እና መላክ

ደንበኞቻን ወደ ግሪክ ሲመጡ ወጫቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በደንበኞቻችን ጥያቄ እና ምርጫ መሠረት የተጠየቋቸውን ዕቃዎች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ደኅንነታቸው እና ሥርዓታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲላኩ እናደርጋለን፡፡ ለደንበኞቻችን ተመጣጣኝ ዋጋ እና ለንዋያተ ቅድሳቱ አያያዝ የሚመቸውን የመላኪያ ሁኔታውን በመገምገም ወደተፈለገው አድራሻ መላክ፡፡

የማማከር አገልግሎት መስጠት

የቤተክርስቲያን አገልጋይ ደንበኞቻችን ለሚያጋጥማቸው ማንኛውም ነገር ሁሉ የምክር አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ ደንበኞቻችን ወደ ግሪክ የመምጣት ዓላማ ካላቸው በጉዞ ድርጅታችን አማካኝነት እገዛ እና ምክር እንሰጣለን፡፡ በተጨማሪም በግሪክ ሀገር የሚመረቱትን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዴት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረድ እንደሚቻል ምክክሮችን እና ሁኔታቾውን እናመቻቻለን፡፡